wass

Wass Insurance S.C

(Under Formation)

Wass Insurance S.C

Under Formation

FAQS

አክስዮንን በተመለከተ

መግዛት የሚችሉት ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን
አንድ ሰው መግዛት የሚችለው አነስተኛው የአክሲዮን ብዛት በብር 100,000.00 ብር በቁጥር ደግሞ 5 ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ብዛት በብር 20,000.000.00 ብር በቁጥር ደግሞ 1,000 ነው።

አከፋፈል
የመጀመሪያ ፊርማ ከተፈረሙው ጠቅላላ አክሲዮን ዉስጥ 25% ከዚያ በላይ ወይም በሙሉ።

የአገልግሎት ክፍያ
የአገልግሎት ክፍያ የፈረሙትን አክሲዮን ጠቅላላ ዋጋ 5%።

የአክሲዮን ሽያጭ

የአክሲዮን ሽያጭ የሚካሄደው በሁሉም የአዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ቅርንጫፎች ነው፡፡

መግዛት የሚችሉት ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን


አንድ ሰው ከኢንሹራንስ ካፒታል ውስጥ ለብቻቸውም ሆነ ከባለቤታቸው ወይም እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ ልጆች ጋር መግዛት የሚችሉት ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን የተፈረመ ጠቅላላ አክሲዮኖች 5%/አምስት በመቶ/

ስለ-ተደማጭነት

 

ማንኛውም ፈራሚ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚገዙት የአክሲዮን መጠን ተደምሮ በኢንሹራንሱ የሚኖራቸው ጠቅላላ አክሲዮን ከኢንሹራንሱ ካፒታል ውስጥ 2%/ሁለት በመቶ/ እና ከዛ በላይ የሚሆን ከሆነ ተደማጭነት ያለው ባለአክሲዮን ስለሚያደርጋቸው ግዢው መጀመሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መፅደቅ ይኖርበታል፡፡

የመድን ሥራ አዋጅ

 

በመድን ሥራ አዋጅ ቁጥር 746/2004 መሠረት በአንድ ኢንሹራንስ ተደማጭነት ያላቸው ከተፈረመው ጠቅላላ አክሲዮን 2% /ሁለት በመቶ/ እና ከዚያ በላይ ያላቸው/ ባለአክሲዮኖች በሌላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ለመግዛት አይችሉም፡፡ ስለሆነም ፈራሚ ባለአክሲዮኖች አክሲዮን ለመግዛት ሲፈርሙ በሌላ ኢንሹራንስ ተደማጭነት ያላቸው ባለአክሲዮን አለመሆናቸው የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

ድርጅቶች

 

ፈራሚ ባለአክሲዮን ድርጅት ከሆኑ የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በሙሉ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የመመሥረቻ ጽሑፍ ወይም ሌላ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ኮፒ በግዢ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች መካከል አንድ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቢኖር ፤ በድርጅቱ የተፈረመውን አክስዮን ጠቅላላ ዋጋ ወደ አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ በተላለፈ የውጪ ምንዛሬ በዕለቱ ባለው የባንኩ የመግዣ ዋጋ ተሰልቶ መከፈል ይኖርበታል፡፡

አክሲዮን መግዛት ቢፈልጉ

በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች የዋስ ኢንሹራንስ አክሲዮን መግዛት ቢፈልጉ ዋስ ኢንሹራንስ ሂሳብ በከፈተባቸው ባንኮችና ቅርንጫፎቻቸው በሙሉ አክሲዮን መግዛት የሚቻል ሲሆን በኢትጵያ ብሔራዊ በንክ መመሪያ “SIB/49/2020’’ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የውጭ ምንዛሪ ገንዘቦች የአሜሪካን ዶላር፣ ዩሮ እና እንግሊዝ ፓውንድ አክሲዮኑን መግዛት ይቻላል፡፡

ዝቅተኛው መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን

ዝቅተኛው መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ግዥ ብር20,000,000.00 (ሃያ ሚሊዮን ብር) ሆኖ በተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አስቀድሞ በተፈረመ የአክሲዮን ግዥ ላይ 5% (አምስት በመቶ) መክፈል ይኖርበታል፡፡

አከፋፈል

የዋስ ኢንሹራንስ በፍጥነት ገበያውን ለመቀላቀል እየሰራ በመሆኑ ክፍያው ባለአክሲዮኑ በተመዘገበበት ወቅት መፈፀም ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ባለአክሲዮኑ በምዝገባ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ለመካፈል ካልቻለ ግማሹን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በቅድሚያ በምዝገባ ወቅት ይከፍላል፡፡ ቀሪውን 75% ክፍያ በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ የአገለግሎት ክፍያ ያለመቆራረጥ ቃል በተገባው የአክሲዮን መጠን ላይ ተሰልቶ በቅድሚያ መክፈል አለበት፡፡

አክሲዮኑን ሲገዙ ዋናውን የአክሲዮን መግዣ በዝግ ሂሳብ፤ የአገልግሎት ክፍያውን 5% (አምስት በመቶ) ደግሞ በተንቀሳቃሽ ሂሳብ ዋስ ኢንሹራንስ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ በከፈተበት ባንክ ማለትም አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፤አቢሲንያ ባንክ፤አዋሽ ባንክ፤የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ያደርጋሉ፡፡

ክፍያው የሚፈጸመው በእለቱ የውጭ ምንዛሪ መግዣ መጠን ተሰልቶ ሲሆን ወደ ዋስ ኢንሹራንስ ሂሳብ ሂሳብ ገቢ የሚደረገው ደግሞ ከባንክ ለባንክ በሆነ ለግዢው አገልግሎት ብቻ የተላከ መሆን ይኖርበታል፡፡

በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አካውንት ላላቸውም

በተጨማሪም በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ አገር ዜጎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያውቀው በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ አካውንት ካላቸውም ከሂሳባቸው የአክሲዮን ግዥውን መፈጸም ይችላሉ፡፡

ገንዘብ ያስተላለፉባቸውን የባንክ ማስረጃዎች በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ መሆናቸውን ከሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይንም በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ በባለቤትነት በያዙት ድርጅት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለዚህም ማስረጃ በማቅረብ የአክሲዮኝ ግዥ ፎርሙን በአካል ወይንም በወኪል በመቅረብ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ወደ ሂብ ገቢ ከተደረገ በኋላ በባንክ የገቢ ደረሰኞች ምትክ፤ የዋስ ኢንሹራንስ የአክሲዮን መግዣና የአገልግሎት ክፍያ መቀበያ ደረሰኞችን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መመሪያ “SIB/49/2020’’ መመልከት የሚቻል መሆኑን እየገለጽን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ቢኖርዎ በስልክ ቁጥሮቻችን ብትደውሉልን እንዲሁም በኢሜል አድራሻችን ብትፅፉልን ማብራሪያ ለመስጠት ዝግጁ መሆናችንን እንገለጻለን፡፡

የአክስዮን ግዢ ፎርም

በዚህ ጥንድ ዓላማዎችን ይዞ በተነሳው ዋስ ኢንሹራንስ አ.ማ አክሲዮን እንዲገዙ በአክብሮት እየጋበዝን የአክሲዮን አሻሻጥና መግለጫዎች፤የአክስዮን መግዣ ቅፅና የአገልግሎት መክፈያ ቅፅን ከዚህ በታች በሚገኘው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ ወይንም በመደወል ማግኘት እንደሚችሉ ለመግለጽ እንወዳለን ፡፡

ሂደቶች

  • ቅጹን ካወረዱ በኋላ ቅጹን ይሙሉ
  • የክፍያ መጠን በ ተዘረዘሩት ባንኮች ይፈጽሙ
  • አስፈላጊ ሰነዶችን ያያይዙ (የተጠናቀቀ ቅጽ፣ ደረሰኝ እና መታወቂያ)
  • በአግባቡ ተሞልቶ እና ተፈርሞ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከዋሽንግቶን አደባባይ ወደ ደንበል ፖሊስ ጣቢያ በሚወስደው መንገድ 30 ሜትር ላይ NK ህንጻ ቢሮ ቁጥር 306 እና 307 ፕሮጀክት ጽ/ቤት መቅረብ አለበት።

     

    ለህዝብ አክሲዎን ለመሽጥ የቀረበ መግለጫ

     መግለጫ አሳይ

    ለግለሰብ 

    ለግለሰብ ቅጽን አውርድ

    ለድርጅት

    ለድርጅትቅጽን አውርድ

    ለግለሰብ እና ለድርጅት

    ለግለሰብ እና ለድርጅት