wass

Wass Insurance S.C

(Under Formation)

Wass Insurance S.C

Under Formation

About Us

Why you Shold Choose Us ?

Wass Insurance is under formation with a principal aim of providing the best health focused insurance policy and other insurance business , and maximize the return to shareholders investment through efficient insurance services provision.

Provide

Provide the best health focused insurance policy.

Maximize

Maximize the return to shareholders investment.

Reverse

Reverses the traditional insurance model.

Many more

Different other insurance business.

አቶ ሄኖክ ተካ

የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢና አስተባባሪ

አቶ ሄኖክ ተካ የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢና አስተባባሪ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ ያጠናቀቁ ሲሆን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በፋርማሲስትነት እና መምህርነት ፣ በቀድሞ የመድኃኒት ፈንድ እና አቅርቦት ኤጀንሲ በፋርማሲቲካልስ ኳንቲፊኬሽን ኦፊሰርነት ፣በአንዱ የኬሚካል አስመጪ ድርጅት ማርኬቲንግ ሥራ አስኪያጅነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ድሮጋ ፋርማ እና ኤማ ኮንስትራክሽን ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ትረስት ፋርማሲቲካልስ ማኑፋችቸሪን ኃላ.የተ.የግ.ማ. በማቋቋም እየመሩ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር አብዲ ኤርሞሎ

የአደራጅ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ

ዶ/ር አብዲ ኤርሞሎ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት አገልግለዋል ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንጎልና ህብረሰረሰር ቀዶ ጥገና የስፔሻላይዜሽን ትምርህታቸውን ለ5 አመታት የተከታተሉ ሲሆን በአሁን ወቅት በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንጎልና ህብረሰረሰር ቀዶ ጥገና እያገለግሉ ነው። በተጨማሪም ድሮጋ ፋርማ እና ኤማ ኮንስትራክሽን እና ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ.ማህበር ትረስት ፋርማሲቲካልስ ማኑፋችቸሪን ኃላ.የተ.የግ.ማ. በማቋቋም እየመሩ ይገኛሉ፡፡

አቶ አማረ ሃበ

የአደራጅ ኮሚቴ አባል እና የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ

አቶ አማረ ሃበ የአደራጅ ኮሚቴው አባልና የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ ቢ.ኤ. ስኮትላንድ ከሚገኘው ከግላሰጎው ዩኒቨርስቲ ከዲቨሎፕመንት ፖሊሲ ድኀረ ዲግሪ ዲፕሎማ/ Post Graduate Diploma እና እንግሊዝ አገር ከሚገኘው ኬንት ዩኒቨርስቲ በዲቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም ከዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በሕግ ዲግሪ በእጅግ በጣም ከፍተኛ ማዕረግ ያጠናቀቁ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስነ-ልቦና ትምህርት ክፍል የሥነ ልቦና አማካሪነት/Counseling Psychology/ በማስተርስ ዲግሪ የመመረቂያ ጽሁፍ ይቀራቸዋል፡፡ በስራ ልምድም በኢኮኖሚ ፕላን ኢኮኖሚክስት የዋጋ ጥናት ፖሊሲ ኢንስቲትዩት ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣ በንግድ ሚኒስቴር የውጭ ንግድ ማስፋፊያ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የአንዱ የመድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ አክሲዮን ማህበር በዋና ሥራ አስኪያጅነት ለ8 ዓመታት ሰርተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሶስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በአራቱ ደግሞ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው የሰሩ ሲሆን በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት በቦርድ አባልነት አገልግለዋል፡፡ ላለፉት 7 ዓመታትም የዘመን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርና (3 ዓመት) የቦርድ አባል (3 ዓመት ከ7 ወር) ያገለገሉ ሲሆን በቅርቡ ተቋቁሞ የኢንሹራንስ ኢንዱስትውን የተቀላቀለው የዘመን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢና አስተባባሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡